የዚህ ዓመታዊ መጽሔት ዋነኛ ዓላማ ሀገራዊ ቋንቋዎቻችንን በጋራ ለማሳደግና ለማልማት እንችል ዘንድ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ነው።
በ2ኛ እትማችን እንደቀድሞው እትም የተለያዩ ጉዳዮችን ለንባብ ለማብቃት ሞክረናል። ከነዚህም ውስጥ ለሀገራዊ ቋንቋዎች ልማትና ዕድገት ጥረት ካደረጉ ግለሰቦች ጀምሮ በመንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካይነት በተለያዩ አካባቢዎች የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን ጭምር በመጠኑ እናስቃኛለን። የሀገራዊ ቋንቋዎች ጉዳት የሚያስከትለውን ችግርና የአፍ መፍቻ ቋንቋ ትምህርትን ጥቅም አስመልክቶ ከምሁራን የቀረቡ ጽሁፎችን አካተናል።

Language Matters 2  ነሐሴ 2005